ስለ ቤተክርስትያኗ አመሰራረት

በስመ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

በመላው አለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሙሉ!

ከሁሉም በማስቀደም የናታችን የቅድስተ ቅዱሳን የኪዳነ ምሕረት በረከቷ ከእናንተና ከመላ ቤተሰቦቻችሁ ጋር አድሮ ይኑር በማለት በበረከት ጥሪ ላይ እንድትሳተፉ የሚያደርግ መልእክታችን ይድረሳችሁ እንላለን!

በደብረ ማርቆስ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ የምትገኘው፣ በአፄ ገብረመስቀል ዘመነ መንግስት በ530 ዓ.ም. የተመሰረተችው፣ ድንቅ ድንቅ ታምራትን የምታደርገው፣ አሁንም በማድረግ ላይ ያለችው እንተ ይእቲ ደብረ ሲና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከመጥበቧ የተነሳ በዚህ ዘመን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ባለመቻሏ ዘመኑን የዋጀ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ተነስተናል። ስራችንንም የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል።