በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ ደብረሲና ግምጃቤት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስትያን ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ባህር ዳር ቅርንጫ

በስመ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

በመላው አለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሙሉ!

ከሁሉም በማስቀደም የናታችን የቅድስተ ቅዱሳን የኪዳነ ምሕረት በረከቷ ከእናንተና ከመላ ቤተሰቦቻችሁ ጋር አድሮ ይኑር በማለት በበረከት ጥሪ ላይ እንድትሳተፉ የሚያደርግ መልእክታችን ይድረሳችሁ እንላለን!

በደብረ ማርቆስ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ የምትገኘው፣ በአፄ ገብረመስቀል ዘመነ መንግስት በ530 ዓ.ም. የተመሰረተችው፣ ድንቅ ድንቅ ታምራትን የምታደርገው፣ አሁንም በማድረግ ላይ ያለችው እንተ ይእቲ ደብረ ሲና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከመጥበቧ የተነሳ በዚህ ዘመን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ባለመቻሏ ዘመኑን የዋጀ አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ተነስተናል። ስራችንንም የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል።

የሕንፃ ቤተክርስቲያኑን መሰረት ለማውጣት አብዛኛውን የግምባታ ግብአቶች አሟልተን ግምባታውን በይፋ ለማስጀመር ከዚህ ቀጥሎ ተዘርዝረው የሚገኙትን ግብአቶችን ማለትም
1ኛ. ባለ10 ቤርጋ ብረት በፍሬ 1816
2ኛ. ባለ12 ቤርጋ ብረት በፍሬ 695
3ኛ. ባለ16 ቤርጋ ብረት በፍሬ 3186
4ኛ. 350 ኩንታል ጥራቱ አስተማማኝ የተባለለት ሲሚንቶ በጽኑ የሚያስፈልግ መሆኑ በህንፃ አሰሪው ቴክኒካል ኮሚቴ የተጠየቀ በመሆኑ እነዚህን ግብአቶች ለማሟላት የገንዘብ ድጋፍ በእጅጉ አስፈላጊ ሆኗል።

እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊትን "የምመሰገንበትን ቤት የሚሰራልኝ ከአብራክህ የሚወጣው ልጅህ ሰሎሞን ነው" ብሎ እንደመረጠው (መጸሐፈ ዜና መዋዕል ምዕራፍ 6 ቁጥር 9) እርስዎም ለስጋዎ እርካታ ለነፍስዎ ረፍት የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት መርጥዎታልና ሀቅምዎ የፈቀደውን ሁሉ እንዲያደርጉ በወላዲት አምላክ ስም እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና "እያንዳንዱ በልቡ ለማድረግ እንዳሰበ ይስጥ" የሚለውን ቅዱስ ቃል በማስቀደም ከመለገስ የማይታጠፍ እጅዎን እንዲዘረጉልን እንጠይቃለን።

እግዚአብሔር አምላክ  ቤተሰብዎንና ህይወትወን ይባርክ!

ማሳሰቢያ: በህንጻ አሰሪ ኮሚቴ የሂሳብ ቁጥርን በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000018047547
ወይም
በቡና ባንክ ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ለምትፈልጉ 1369528000165
ለግምጃ ቤት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ብላችሁ ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።